ድርጅቱ የተመሠረተው በ2006 ዓ.ም በአቶ ብርሃን ዲባባ እና በሁለት መሥራች አባላት ነው። ይህ ድርጅት የሚያመርታቸው ምርቶች አጠቃላይ የአልባሳት አይነቶች ናቸው።
ተጨማሪYohannes Teshome
የኛ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር
“የኛ ሁሌም የኛ የሁላችንም ነው!!” በሚል መሪ ቃል የሚታወቀው የኛ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የሚገኙ እና በትምህርት ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑትን፣ እንዲሁም መካከለኛውን የኅብረተ ሰብ ክፍሎች በገንዘብ አስተዳደር እና አጠቃቀም እና በተለያዩ ሥልጠናዎች በማገዝ የኑሮና አኗኗር ለውጥን ለማምጣት እና ለመሥራት የተቋቋመ የገንዘብ ቁጠባና …
ተጨማሪ“ዛሬ በመቆጠብ ነገን በተሻለ ህይወት ይኑሩ” – አፍሪካ ቪሌጅ ፋይናንሽያል ሰርቪስስ አ.ማ.
አፍሪካ ቪሌጅ ፋይናንሽያል ሰርቪስስ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 626/2009 መሠረት ተቋቁሞ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በማግኝት እ.ኤ.አ. ከ1999 ጀምሮ በኦሮሚያና በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ውስጥ ፋይናንስ ነክ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ የሚገኝ የፋይናንስ ተቋም ነው።
ተጨማሪመንግሥቱ የቆዳ ውጤቶች
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ መንግሥቱ ሺፈራው በ2008 ዓ.ም. ነው። አቶ መንግሥቱ በቆዳ ውጤቶች፣ በቀበቶ እና በተለያዩ የጫማ ሥራዎች ላይ የሰላሣ ዓመት የሥራ ልምድ አካብተዋል።
ተጨማሪዜድቲኢ አልሙኒየም እና ኢንቲሪየር ዲዛይን ሥራ
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ዘላለም እና በጓደኛቸው መሥራች አባልነተ በ2011 ዓ.ም. ነው። የሚሠራቸው ሥራዎች አጠቃላይ የአሉሚኒየም ሥራዎች፣ የማማከር፣ አጠቃላይ የኢንቲሪየር ዲዛይን (የቤት ውስጥ ስነ ውበት)፣ እንዲሁም የኮንስትራክሽን ሥራዎችን ይሠራል። የድርጅቱ መሥራቾች በዘርፎቹ ከሰባት ዓመት በላይ የሥራ ልምድ አዳብረዋል።
ተጨማሪአልአዛር እና ሄኖክ እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ አልአዛር ዓለም እና በአቶ ሄኖክ በ1996 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የእንጨት እና የብረታ ብረት ሥራዎችን የሚሠራ ድርጅት ሲሆን በነዚህ ሥራዎች ውስጥ ውስጥ የዲዛይን እና ፈኒቸር ሥራዎች ይካተታሉ።
ተጨማሪፋና የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር
ፋና የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ መሥራች አባላት ሐምሌ 13 ቀን፣ 2011 ዓ.ም. በሕጋዊ መንገድ ተመሠረተ።
ተጨማሪድባብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር
ድባብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ሁሉንም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎችን አባል ለማድረግ ዓላማ ይዞ የተቋቋመ የኅብረት ሥራ ማኅበር የፋይናንስ ተቋም ነው።
ተጨማሪእቴጌ ዳቦ እና ብስኩት
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ሳሙኤል በለጠ፣ በሁለት ሴቶች እና አንድ ወንድ መሥራች አባላት በ2010 ዓ.ም. ነው። ይህ ድርጅት የሚያመርታቸው ምርቶች ምግብ እና መጠጥ ሲሆኑ በአሁን ጊዜ በዳቦ፣ ኩኪስ እና ጨው ምርቶች ላይ በስፋት እየሠራ ይገኛል።
ተጨማሪሃበሻ ኢንተርፕረነርስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር
ሃበሻ ኢንተርፕረነርስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 985/09 መሠረት የተቋቋመ ሕጋዊ ድርጅት ነው። የሥራ ፈጣሪዎች በአንድነት የጋራ የሆኑ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮቻቸውን ለመፍታት እንዲችሉም የተቋቋመ ማሕበር ነው፡፡
ተጨማሪ