መንግሥቱ እና ዳዊት ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የተመሠረተው በአቶ መንግሥቱ አባተ በ2009 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎች ጠቅላላ የኮንስትራክሽን ሥራዎች በዋናነት እንዲሁም የተለያዩ የአበባ ማስቀመጫ እቃዎችን በተለያየ መጠን እና ዲዛይን በተጨማሪም የህጻናት መጫወቻዎችን በጥራት ያመርታል።
ተጨማሪYohannes Teshome
“የእኛን ሥራ ብዙ ሰው ይሠራዋል የእኛን ሀሳብ ግን ማንም ሊሠራው አይችልም” ቲኬ ማሽን የመገጣጠም ሥራ
ቲኬ ማሽን የመገጣጠም ሥራ የተመሠረተው በ 2007 ዓ.ም በአቶ ሲሳይ ደጉ እና በጓደኛቸው መሥራች አባልነት ነው። ድርጅቱ የሚሠራው ሥራ ማሽን የመገጣጠም ሥራ (Assembling) ነው። በአጭር ጊዜ ብዙ ማሽኖችን የመገጣጠም እና የማምረት አቅም አለው። ከዚህ በተጨማሪ የአሉሚኒየም ምርቶችን ያመርታል።
ተጨማሪግሪን ሆፕ ሪኒወብል ኢነርጂ
ግሪን ሆፕ ሪኒወብል ኢነርጂ የተመሠረተው በ 2011 ዓ.ም በአቶ አቤል ዘርፉ እና በጓደኛቸው ነው። አረንጓዴ የታዳሽ ኃይል (Green hope Renewable Energy) የሚሠራቸው ሥራዎች በዋናነት የታዳሽ ኃይል ኤሌክትሪክ አቅርቦት (Renewable Energy) የሕንፃ ኤሌክትሪክ መሥመር ዝርጋታ (Building installation) የተለያዩ የኤሌክትሪክ ገመዶች አቅርቦት እንዲሁም ተያያዥ ሥራዎች የጥገና እና የጥሬ እቃ አቅርቦት አገልግሎት ናችወ።
ተጨማሪዘ ኬክ ኮርነር
የተመሠረተው በ 2012 ዓ.ም በሼፍ ብርሐኑ ረጋሳ ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የዳቦ እና የኬክ ምርቶችን የሚያመርት ድርጅት ሲሆን፤ የድርጅቱ መሥራች ከድርጅቱ ምሥረታ በፊት ለሃያ ሦስት ዓመታት በሙያቸው ከትልቅ ድርጅቶች ጋር ተቀጥረው ሲሠሩ ቆይተዋል። ድርጅቱ አጠቃላይ የቤከሪ (ዳቦ፣ ኩኪስ፣ ኬኮች፣ ወዘተ መጋገር) ሥራዎችን የሚሠራ ድርጅት ሲሆን በአሁን ጊዜ ግን የኬክ ሥራዎች ላይ …
ተጨማሪየከፍታ ፓኬጅን ተጠቀመን ጨረታዎች እያሸነፍን ነው – አንዋር ሱሌማን እና ጓደኞቻቸው የስፖንጅ እና ፎም ውጤቶች አምራች
አንዋር ሱሌማን እና ጓደኞቻቸው የስፖንጅ እና ፎም ውጤቶች የተመሠረተው በ 2010 ዓ.ም በአቶ አንዋር እና አራት መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ የተለያዩ ለአልጋ እና ለትራስ የሚሆኑ ስፖንጆችን የሚያመርት ድርጅት ሲሆን፣ በቀን ሁለት መቶ ሀምሳ ትራሶችን የማምረት አቅም አለው።
ተጨማሪዓለም ግዛቸው ልብስ ስፌት
ዓለም ግዛቸው ልብስ ስፌት የተመሠረተው በ 2011 ዓ.ም በ ወ/ሮ ዓለም ግዛቸው የግል ኢንተርፕራይዝ ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የልብስ ስፌት ሥራዎችን የሚሠራ ድርጅት ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የልብስ ስፌት ሥራዎችን የሚሠራ ድርጅት ቢሆንም በብዛት ግን የህጻናት አልባሳትን ነው የሚሠራው። ከአራስ ጀምሮ እስከ ሥራ አራት አመት ለሚገኙ ህጻናት የሚሆኑ ልብሶችን በብዛት ያመርታል።
ተጨማሪመስከረም ክበበው የቤት እና የቢሮ እቃዎች
የተመሠረተው በ 2006 ዓ.ም በወ/ሮ መስከረም ክበበው ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የቤት እና የቢሮ እቃዎች የሚያመርት ድርጅት ሲሆን ይህ ድርጅት በአስራ አምስት ቀን ሶስት መቶ ወንበሮችን በጥራት የማምረት አቅም አለው። እንደ ወንበሮቹ ዲዛይን ቀኑ ሊለያይ ይችላል። ድርጅቱ በአሁን ጊዜ ለዐሥራ አራት ቋሚ እና ሁለት ጊዜያዊ ሠራተኞች የሥራ እድል መፍጠር ችሏል።
ተጨማሪነቢያት አስረሳኸኝ እንጨት እና ብረታ ብረት
ነቢያት አስረሳኸኝ እንጨት እና ብረታ ብረት የተመሠረተው በ 1998 ዓ.ም ነው። የተመሠረተውም በአቶ ነብያት እና ዘጠኝ መሥራች አባላት ነበር። ነገር ግን በተፈጠሩ የተለያዩ አለመግባባቶች እና በነበሩ ብዙ ፈታኝ ሁኔታዎች አንዳንድ አባላት የሥራ ቦታ በመቀየራቸው፣ አንዳንድ አባላት ደግሞ የተሻለ እድል በመፈለጋቸው እና በተለያዩ ምክንያቶች በአሁን ጊዜ ሦስት አባላት ብቻ በድርጅቱ ውስጥ …
ተጨማሪቴዎድሮስ አባይ የኤሌክትሮኒክስ እና ስፖርት እቃዎች አቅራቢ
ድርጅቱ የተመሠረተው በ 2005 ዓ.ም መጨረሻ በአቶ ቴዎድሮስ አባይ ነው። ይህ ድርጅት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እና የስፖርት እቃዎችን የሚያቀርብ ድርጅት ሲሆን የኤሌክትሮኒክስ እና የስፖርት እቃዎችን በበቂ ብዛት እና ጥራት የማቅረብ አቅም አለው።
ተጨማሪውብ ፊኒሺንግ ሶሉሽንስ
ውብ ፊኒሺንግ ሶሉሽንስ የተመሠረተው በ 2011 ዓ.ም በአቶ ካሊድ አብዲ እና ሁለት መሥራች አባላት ነው። ውብ ፊኒሺንግ አጠቃላይ የፊኒሽንግ ሥራዎችን የሚሠራ ድርጅት ነው። ከድርጅቱ ምሥረታ በፊት አቶ ካሊድ ከጓደኞቻቸው ጋር ለሦስት አመት በትውውቅ (በሰው በሰው) ሥራውን ሲሠሩ ከቆዩ በኋላ ተደራጅተን በሙሉ አቅም ብንሠራ ደግሞ የተሻለ ተጠቃሚ እንሆናለን በማለት ነበር ድርጅቱን …
ተጨማሪ