መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ (page 12)

ልምድ እና ተሞክሮ

በዚህ ገጽ ሥር፣ በሥራቸው ውጤታማ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች ተሞክሮ ይቀርባል። ታሪካቸው ከሚወሳው ኢንተርፕራይዞች ጉዞ፣ ለእርስዎ የሚጠቅሙ ተግባራዊ የሆኑ አስተውሎቶች፣ ምክሮች እና ጥቆማዎችን ያገኛሉ። በሥራችሁ ውጤታማ ከሆናችሁ፣ ንገሩንና እዚህ ገጽ ላይ እናወጣችኋለን። ታሪካችሁ ሌሎችን ያስተምራል፣ ቢዝነሳችሁንም ያስተዋውቃል። በ6131 ወይንም በ 0975616161 ደውሉልን።

ማቱት ብዙነሽ እና ጓደኞቻቸው የሕብረት ሥራ ሽርክና ማኅበር

ማቱት፣ ብዙነሽ እና ጓደኞቻቸው የሕብረት ሥራ ሽርክና ማኅበር በአቶ ማቱት ታይሉ እና በሁለት መስራች አባላት 2011 ዓ.ም ላይ ነው የተመሰረተው። የሚያምረተው ምርት የእንጀራ ምርት ነው። ማኅበሩ ሲመሰረት ከነበረው ሦስት አባላት ተነስቶ በአሁኑ ጊዜ ለስድስት ቋሚ እና ስድስት ጊዜያዊ ሠራተኞች የሥራ እድል በመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ተጨማሪ

የእንጨት ሥራ – ታደለ ሱልጣን እና ጓደኞቻቸው የእንጨት ሥራ ህብረት ሽርክና ማህበር

tadele-sultan

ታደለ ሱልጣን እና ጓደኞቻቸው የእንጨት ሥራ ሽርክና ማኅበር የተመሠረተው በ2011 ዓ.ም ግንቦት ወር መጨረሻ ሲሆን  በአሁኑ ወቅት ሁለት ዓመት ሆኖታል። አላማው ሠርቶ ለመለወጥ እና የሥራ እድል በመፍጠር ለሌሎችም የሥራ እድል ማመቻቸት መሆኑን ከመስራች አባላት መካከል አንዱ የሆነው አቶ ታደለ የሺ በላይ ገልጸዋል። አቶ ታደለ ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት ከቤተሰባቸው ጋር …

ተጨማሪ

የእንጨት ሥራ -ሶሊና ሶፋ የቤት እና የቢሮ እቃዎች አምራች

ሶሊና ሶፋ የቤት እና የቢሮ እቃዎች አምራች የተመሰረተው በ2001 ዓ.ም በአቶ አብይ ወልደሐና እና በአምስት መሥራች አባላት ነው። በ2001 ዓ.ም ቢመሰረትም ምርት በጥሩ ሁኔታ ማምረት የጀመረው ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ነው። በአሁን ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ከሚባሉ እና አንጋፋ ሶፋ አምራች ድርጅቶች ውስጥ አንዱ ነው። በአዲስ አበባ በሦስት ቅርንጫፎች በጎተራ፣ ጉርድ …

ተጨማሪ

የልብስ ስፌት ሥራ – ቅድስት ሰለሞን ልብስ ስፌት

ቅድስት ሰለሞን ልብስ ስፌት የተመሰረተው 2005 ዓ.ም በወ/ት ቅድስት ሰለሞን ነው። ድርጅቱ ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ በመልካም የእድገት ሁኔታ ምርት በማምረት ሂደት ላይ እንደሚገኝ የድርጅቱ መሥራች አባል ወ/ት ቅድስት ሰለሞን አስረድታለች። የመስራቿ የልብስ ስፌት እውቀት እንዲሁም የሥራ ልምድ ተደምሮ ድርጅቱ ሲመሰረት ከነበረው አንድ ማሽን አሁን ላለው አምስት ማሽን እና አራት …

ተጨማሪ

የድር እና ማግ ሥራ – ሪል ድር ማጠንጠኛ

ሪል ድር ማጠንጠኛ የተመሰረተው 2005 ዓ.ም ሲሆን መስራቾቹም ሦስት  አባላት ናቸው። ድርጅቱ ሁለት ዓመታት ያህል በጥሩ ሁኔታ ሲያመርት መቆየቱን የድርጅቱ መስራች አባል የሆነው አቶ ሀብታሙ አስረድቷል። የአቶ ሀብታሙ በሙያው ተገቢ የሥራ ልምድ መኖር፣ እንዲሁም የእህቱ የቴክስታይል ተማሪ መሆን እና በኳሊቲ ኮንትሮል በፋብሪካ ውስጥ ለረጅም ግዜ መሥራት ከባለቤቱ የሒሳብ ሥራ ክህሎት …

ተጨማሪ

“ደንበኞችን ማርካት ዋና የቢዝነስ የማእዘን ራስ ነው”

leather-product

ሳሙኤል ደባልቄ የሌዘር ሥራ ሳሚ የሌዘር ሥራ የተመሰረተው በ 2007 ዓ.ም ሲሆን፣ ድርጅቱ የምርት ሥራ የጀመረው በ2008 ዓ.ም ነው። የድርጅቱ መስራች የሆነው አቶ ሳሙኤል ሲያስረዳ በሙያው የትምህርት እንዲሁም የሥራ ልምድ በመቅሰም ወደ ድርጅቱ ምስረታ እንደመጣ ሳሚ ይናገራል። ሳሚ ሌዘር ሲመሰረት በአንድ ማሽን በራሱ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ሁለት …

ተጨማሪ

“በደንብ የሚያውቁትን ስራ መሥራት ለውጤታማነት ቁልፍ ነው”

ሳሙዔል ሰማኸኝ (ሳሚ ማተሚያ ድርጅት) ሳሚ ሕትመት እና ተያያዥ ሥራዎች የተመሰረተው በ 2011 ዓ.ም ሲሆን፣ የተመሠረተውም የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ በአቶ ሳሙኤል ሰማኸኝ ነበር። ድርጅቱ ሲመሰረት ሥራው ብዙም አስቸጋሪ እንዳልነበረ አቶ ሳሙዔል ይናገራል። የድርጅቱ መስራች የሆነው አቶ ሳሙዔል ወደ ሕትመት ሥራ ከመግባቱ በፊት በአይቲ (IT) ሥራ አራት ዓመት ሲሠራ እንደቆየ ያስረዳል። …

ተጨማሪ

የሚወዱትን የመሥራት እና የፅናት ውጤት

አሰገደች የልብስ ስፌት ሥራ ድርጅት አሰገደች የልብስ ስፌት የተመሰረተው በ 2005 ዓ.ም ሲሆን ድርጅቱ ሲመሰረት በሦስት መስራች አባላት እና በሦስት የልብስ ሲፌት ማሽኖች ነበር።  ድርጅቱ በተመሰረተበት ወቅት ብዙ አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንደ ነበሩ ወ/ሮ አሰገደች ይናገራሉ። እንዲያም ሆኖ፣ እነዚህን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ተቋቋሙ የዘለቀው ድርጅት በተሻለ ደረጃ ምርት ማምረት የጀመረው በ2009 ዓ.ም …

ተጨማሪ

“ዓላማ፣ ትዕግሥት እና ጠንክሮ መሥራት እዚህ አድርሰውናል”

ኃይለገብርዔል፣ ፈረደ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ኃይለገብርዔል፣ ፈረደ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ኅብረት ሽርክና ማኅበር የተመሠረተው 1999 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ነው – በ3,000 ብር ካፒታል። መሥራቾቹ፣ ድርጅቱ ሲመሠረት ብዙ ፈታኝ ሁኔታዎች እንደነበሩ ይናገራሉ። በተለይ የመደራጀት ችግር፣ መነሻ ካፒታል ማጣት፣ ብድር አለማግኘት ፣ የመሥሪያ ቦታ አለመኖር ወዘተ። …

ተጨማሪ