ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባገኘው ፈቃድ መሠረት በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ ለተሰማሩ የማኅበረ ሰብ ክፍሎች በረዥም እና በዐጭር ጊዜ የሚመለሱ የብድር ዐይነቶችን በተለያዩ የዋስትና አማራጮች አቅርቧል።
ተጨማሪፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት
ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም
ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት በ1989 ዓ.ም. ተመሠረተ። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለተቋሙ የሰጠው የፈቃድ ቁጥር MFI/034/2011 ሲሆን የንግድ ምዝገባ ቁጥሩ ደግሞ 06/2/06393/96 ነው። ተቋሙ ከቀደምት ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ውስጥ አንዱ ሲሆን ከ24 ዓመት በላይ የብድርና ቁጠባ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። በአሁኑ …
ተጨማሪየአዲሲቷ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር
ኅብረት ሥራ ማኅበር ማለት ሰዎች የጋራ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ያላቸውን ዕውቀት፣ ጉልበት፣ ጊዜ እና ሀብት በማሰባሰብ ችግሮቻቸውን መፍታት የሚያስችል ቁልፍ መሣሪያ ነው። በዚህ መሠረት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ መሥራች አባላት በሕጋዊ መንገድ የተመሠረተ ማኅበር ነው። መቆጠብ መሰሰት አይደለም!!! ለለውጥ …
ተጨማሪዋን ማይክሮፋይናንስ
ዋን ማይክሮ ፋይናንስ ቀደም ሲል ለታ ማይክሮ ፋይናንስ በመባል ይታወቅ የነበረ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ነው። በብሔራዊ ባንክ ሕግ እና ደንብ መሠረት በአዋጅ ቁጥር 40/1996 (በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 626/2009) የተቋቋመ ሲሆን የማይክሮ ፋይናንስ እና ተያያዥ አገልግሎቶችን ለመስጠት ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ተሰጥቶት ጥቅምት 28 ቀን 1997 (29 October 2004) ዓ.ም. ሥራ ጀምሯል። …
ተጨማሪየካቲት 23 የገንዘብ ቁጠባና ብድር
የካቲት 23 የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኀላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ቁጠባን ባሕል አድርጎ በራስ ገንዘብ ሕይወትን መቀየር ይቻላል ብሎ ያምናል። ይህም ይሳካ ዘንድ መደበኛ እና የፈቃድ ቁጠባ ለአባላቱ ያዘጋጀ ሲሆን ለስድስት ወር በተከታታይ በመቆጠብ ብድር መበደር እንዲችሉ ያደርጋል። በዚህም አባላት የራሳቸውን፣ የቤተሰባቸውን ብሎም የአገራቸውን የእድገት ለውጥ እንዲያፋጥኑ የሚያደርግ ተቋም ነው።
ተጨማሪቤተ-ሐበሻ ቁጠባ እና ብድር ኀላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር
ኅብረት ሥራ ማኅበር ሰዎች የጋራ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ያላቸውን ዕውቀት፣ ጉልበት፣ ጊዜ እና ሀብት በማሰባሰብ ችግሮቻቸውን መፍታት የሚያስችል ቁልፍ መሣሪያ ነው። በዚህ መሠረት ቤተ-ሐበሻ ቁጠባ እና ብድር ኀላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ መሥራች አባላት በሕጋዊ መንገድ የተመሠረተ የኅብረት ሥራ ማኅበር ነው።
ተጨማሪጊዜ የገንዘብ ቁጠባና ብድር
ጊዜ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በሕግ ታውቆ በምዝገባ ቁጥር ቦሌ/1/1234/2013 የተመዘገበ ለመሆኑ የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ወረቀት በኅዳር 15 ቀን፣ 2013 ዓ.ም. ተሰጥቶት ሥራ ጀምሯል።
ተጨማሪአማራጭ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር
አማራጭ የኮድ 3 ሜትር ታክሲ እና የኮድ አንድ ታክሲ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ኅብረተ ሰቡ ከሚያገኘው ገቢ ላይ የተወሰነ ገንዘብ በመቆጠብ ራሱን በራሱ እንዲረዳና የቁጠባን ባሕል በማዳበር ፈጣን የሆነ የብድር አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል ታኅሳስ 9 ቀን፣ 2014 ዓ.ም. በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 50 አባላትን …
ተጨማሪቤተል የገንዘብ ቁጠባና ብድር
ቤተል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኀበር የተቋቋመው በኢትዮጵያ የኀብረት ሥራ ማኅበር አዋጅ መሠረት በቁጥር 985/2009 ሲሆን፤ ሕጋዊ ሰውነት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኀብረት ሥራ ኤጀንሲ በነሐሴ 2005 ዓ.ም. ፈቃድ አግኝቶ በሥራ ላይ ይገኛል። “ቤተል ውስጥ ሁላችንም አለን!!”
ተጨማሪእስታቴር ገንዘብ ቁጠባ እና ብድር
እስታቴር ገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአዲስ አበባ የተቋቋመ ሲሆን ዋናው ቢሮውም በኮልፌ አጠና ተራ ይገኛል።
ተጨማሪ