መነሻ / Tag Archives: ethiopia (page 13)

Tag Archives: ethiopia

“በደንብ የሚያውቁትን ስራ መሥራት ለውጤታማነት ቁልፍ ነው”

ሳሙዔል ሰማኸኝ (ሳሚ ማተሚያ ድርጅት) ሳሚ ሕትመት እና ተያያዥ ሥራዎች የተመሰረተው በ 2011 ዓ.ም ሲሆን፣ የተመሠረተውም የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ በአቶ ሳሙኤል ሰማኸኝ ነበር። ድርጅቱ ሲመሰረት ሥራው ብዙም አስቸጋሪ እንዳልነበረ አቶ ሳሙዔል ይናገራል። የድርጅቱ መስራች የሆነው አቶ ሳሙዔል ወደ ሕትመት ሥራ ከመግባቱ በፊት በአይቲ (IT) ሥራ አራት ዓመት ሲሠራ እንደቆየ ያስረዳል። …

ተጨማሪ

የሚወዱትን የመሥራት እና የፅናት ውጤት

አሰገደች የልብስ ስፌት ሥራ ድርጅት አሰገደች የልብስ ስፌት የተመሰረተው በ 2005 ዓ.ም ሲሆን ድርጅቱ ሲመሰረት በሦስት መስራች አባላት እና በሦስት የልብስ ሲፌት ማሽኖች ነበር።  ድርጅቱ በተመሰረተበት ወቅት ብዙ አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንደ ነበሩ ወ/ሮ አሰገደች ይናገራሉ። እንዲያም ሆኖ፣ እነዚህን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ተቋቋሙ የዘለቀው ድርጅት በተሻለ ደረጃ ምርት ማምረት የጀመረው በ2009 ዓ.ም …

ተጨማሪ

በኮቪድ-19 ለተጎዱ ኢንተርፕራይዞች የሚውል 207 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ስምምነት ተፈረመ

ዛሬ በገንዘብ ሚኒሰቴር በተደረገ የፊርማ ስነ-ሰርዓት ላይ በኢትዮጰያ መንግስት እና በዓለም ባንክ የ907 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ። ከዚህ ውስጥ 200 ሚሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ውስጥ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የሚውል ነው። የ200 ሚሊዮን ዶላሩ ድጋፍ ዒላማ ያደረገው በተለይ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ክፉኛ ተጎድተው፣ ነገር ግን ቢደገፉ በሥራቸው አዋጭ ሆነው …

ተጨማሪ

ኢሜይልን እንዴት አድርገን ለቢዝነስ መጠቀም እንችላለን?

email-business

በዚህ ዘመን መልዕክቶችን በቴሌግራም፣ በፌስቡክ ሜሴንጀር፣ በዋትስአፕ፣ በቫይበር፣ በዊቻት እና በመሳሰሉት መለዋወጥ ይቻላል፤ ቢሆንም ኢሜይል ለቢዝነስ ወሳኝ እና ከሌሎች ኢንተርኔትን ተጠቅመን ከምንልካቸው መልዕክቶች የበለጠ መደበኛ (formal) የሆነ የመልዕክት መለዋወጫ ዘዴ ነው። በተለይ ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ስንሠራ (ጨረታም ሆነ የኢምፖርት/ኤክስፖርት ቢዝነስ) በኢሜይል በትክክል መልዕክት መለዋወጥ መቻል በጣም አስፈላጊ ነው። አንዳንድ …

ተጨማሪ

ከፍታ ማዕከል በስዊድን እና ኔዘርላንድስ ኤምባሲዎች እና የአውሮፓ ኅብረት ልዑካን ቡድን ተጎበኘ

kefta-april-delegates-visit

ሐሙስ መጋቢት 30፣ 2013 ዓ.ም የከፍታ ማዕከል ከስዊድን እና ከኔዘርላንድስ ኤምባሲዎች፣ እንዲሁም ከአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያ ልዑክ የመጡ ጎብኚዎችን አስተናግዷል። ጉብኝቱ የተካሄደው የከፍታ አጋር በሆነው የኔዘርላንድስ በጎ አድራጎት ድርጅት ኤስኤንቪ (SNV) እና ከሴቶች እና ወጣቶች ጋር በተያያዘ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሊዌይ (LI-WAY) አስተባባሪነት ነው። በጉብኝቱ ወቅት ለተገኙት በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር ሃንስ …

ተጨማሪ

“ዓላማ፣ ትዕግሥት እና ጠንክሮ መሥራት እዚህ አድርሰውናል”

ኃይለገብርዔል፣ ፈረደ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ኃይለገብርዔል፣ ፈረደ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ኅብረት ሽርክና ማኅበር የተመሠረተው 1999 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ነው – በ3,000 ብር ካፒታል። መሥራቾቹ፣ ድርጅቱ ሲመሠረት ብዙ ፈታኝ ሁኔታዎች እንደነበሩ ይናገራሉ። በተለይ የመደራጀት ችግር፣ መነሻ ካፒታል ማጣት፣ ብድር አለማግኘት ፣ የመሥሪያ ቦታ አለመኖር ወዘተ። …

ተጨማሪ

ቴሌግራም (Telegram) እና ቢዝነስ

telegram

ቴሌግራም (Telegram) በአገራችን በጣም ተወዳጅ የሆነ የመልዕክት መለዋወጫ (Instant Messaging) አፕ/መተግበሪያ ነው። ተወዳጅ ከሆነበት ምክንያት አንዱ በአነስተኛ ዳታ መጠቀም መቻሉ ነው። ቴሌግራምን በስልካችንም ሆነ ከስልካችን አካውንት ጋር አገናኝተን በኮምፒውተራችን ላይ መጠቀም እንችላለን። ቴሌግራም በተለይ አገራችን ውስጥ ከሌሎች የመልዕክት መለዋወጫ (Instant Messaging) አፖች/መተግበሪያዎች በላቀ ሁኔታ ተወዳጅ ስለሆነ ለለቢዝነሶች ከፍተኛ ጥቅም አለው። …

ተጨማሪ

ሊንከዲን (LinkedIn) እና ቢዝነስ

LinkedIn - Business

ሊንከዲን (LinkedIn) በማይክሮሶፍት ባለቤትነት የተያዘ ለቢዝነሶች፣ ለፕሮፌሽናሎች፣ ለሥራ ፈላጊዎች እና ቀጣሪዎች የተቋቋመ የማኅበራዊ ድረ ገጽ ነው። አባል ለመሆን ምንም አይነት ክፍያ አያስፈልግም። ግን የአባልነት ዓይነቱን ወደ ፕሪሚየም (premium) ከፍ ማድረግ ከፈለግን እና ማስታወቂያ ማውጣት ከፈልግን ግን ከፍያ ያስከፍለናል። ከዚህ በታች የተጠቀሱት አግልግሎቶች በሙሉ በነጻ ናቸው።

ተጨማሪ