እሸቱ እና ሣምሪ ልብስ ስፌት አገልግሎት የተመሠረተው በአቶ እሸቱ ደጉ እና በባለቤታቸው በወ/ሮ ሣምራዊት መሥራች አባልነት በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የልብስ ስፌት ሥራዎችን ይሠራል። የዚህ ድርጅት መስራቾች በልብስ ስፌት እና በፋሽን ዲዛይን ሥራ የዐሥራ ሰባት ዓመት ድምር ልምድ አላቸው።
ተጨማሪTag Archives: experience sharing
ግሬስ ኢንጂነሪንግ
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ተሾመ ደበሌ እና በአራት መሥራች አባላት በ2009 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎችን አጠቃላይ የማሽነሪ እና የብረታ ብረት ሥራዎች ናቸው።
ተጨማሪናሆም፣ እሴተ እና ጓደኞቻቸው የኮንስትራክሽን እና የግንባታ ዲዛይን አማካሪ ድርጅት
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ማርቆስ አሠፋ እና በአራት መሥራች አባላት በ2012 ዓ.ም ነው። ደርጅቱ የኮንስትራክሽን፣ የዲዛይን ሥራዎችን እና ተያያዥ የማማከር አገልግሎቶች ይሠጣል።
ተጨማሪእንደ እናት እንጀራ ማከፋፈያ
የተመሠረተው በወ/ሮ ኤልሻዳይ ተካልኝ በግል ኢንተርፕራይዝነት በ2012 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ የሚያቀርበው አገልግሎት የእንጀራ ምርት አገልግሎት ነው።
ተጨማሪያሬድ እና ጓደኞቹ ቡና እና ቁርስ
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ያሬድ ጌታሁን እና በአራት መሥራች አባላት በ2012 ዓ.ም አጋማሽ ነው። ድርጅቱ የሻይ እና ቡና፣ የቁርስ እና ምሳ እንዲሁም እንዳንድ ቀለል ያሉ የሻይ ሰዓት አገልግሎቶችን በተለያዩ ስብሰባዎች ላይ በመገኘት አገልግሎት ይሰጣል።
ተጨማሪዮብ ፈርኒቸር
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ዮናስ ቢያድግልኝ በ2005 ዓ.ም. ነው። ይህ ድርጅት አጠቃላይ የእንጨት ሥራዎችን በጥራት ያመርታል።
ተጨማሪሬድዋን ተማም የቤት እና የቢሮ እቃዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት
ድርጅቱ የተመሠረተው በ 2005 ዓ.ም. በዐሥር መሥራች አባላት ሲሆን አሁን ላይ ግን ሦስት አባላት ብቻ በድርጅቱ ውስጥ ይገኛሉ። ድርጅቱ በአሁን ጊዜ የኪችን ካቢኔቶችን በዋናነት በማምረት ላይ ይገኛል።
ተጨማሪሙስጠፋ ጀማል ብረታ ብረት
ሙስጠፋ ጀማል ብረታ ብረት ድርጅት በአቶ ሙስጠፋ ጀማል ባላቤትነት የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ ነው የተመሠረተው። ድርጅቱ በዋናነት የፍሬንች በሮችን የሚሠራ ሲሆን በተጨማሪም አጠቃላይ የብረታ ብረት ሥራዎችን ይሠራል።
ተጨማሪፊልጶስ፣ ኤደን እና ታረቀኝ ሽርክና ማኅበር
ፊልጶስ፣ ኤደን እና ታረቀኝ ሽርክና ማኅበር የተመሠረተው በ2004 ዓ.ም በአቶ የማነ አብርሐም እና ሦስት መሥራች አባላት ሲሆን ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች አቸቶ (ኮምጣጤ) እና የለውዝ ቅቤ ናቸው። ድርጅቱ በቀን አንድ ሺህ ሊትር አቸቶ የማምረት አቅም አለው።
ተጨማሪጎዳዳ፣ መርጊያ እና ጓደኞቻቸው የሻማ ውጤቶች ማምረቻ
ድርጅቱ የተመሠረተው በ 2006 ዓ.ም በዐሥራ ዘጠኝ መሥራች አባላት ሲሆን አሁን ላይ ግን በዘጠኝ መሥራች አባላት እየሠራ ይገኛል። ከአባላቱም መካከል ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ይገኙበታል፡፡ ድርጅቱ የተለያዩ ሻማዎች በተለያየ ዲዛይን ያመርታል እንዲሁም የጧፍ ምርቶችን ያመርታል።
ተጨማሪ