ኤርታሌ ማኑፋክቸሪንግ ማሽነሪ እና ግንባታ ግብዓት አምራች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተመሠረተው በአቶ በፍርዱ ሠይፉ እና በዐሥራ አራት አባላት 1996 ዓ.ም መጨረሻ ነበር። ይህ ማኅበር የማኑፋክቸሪንግ እና የኮንስትራክሽን ሥራዎች የሚሠራ እንዲሁም ሰላሳ የወፍጮ ማሽን ሞልዶች ለወፍጮ ድንጋይ ማምረቻ እና በጣም ዘመናዊ የብረት ማቅለጫ ያለው ድርጅት ነው።
ተጨማሪYohannes Teshome
ታደለ ፋስት ፉድስ
ታደለ ፋስት ፉድስ በ 2010 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ነው የተመሠረተው። ድርጅቱ ፈጣን (ቶሎ የሚደርሱ) ምግቦችን በሁለት ደቂቃ ውስጥ የሚያደርስ ድርጅት ነው። ይህ ድርጅት የተለያዩ ሳንድዊቾችን ለተገልጋይ በሁለት የተለያየ መንገድ ያቀርባል፦ ምግቡን ይዞ መሄድ የሚፈልግ ይዞ ይሄዳል፤ እዛው አረፍ ብሎ መመገብ የሚፈልግ ደግሞ ይመገባል። ታደለ ፋስት ፉድስ ፈላፈል ሳንድዊችን በአዲስ አበባ …
ተጨማሪብሩክ እና አስማረች ኮንስትራክሽን እና ማኑፋክቸሪንግ
ብሩክ እና አስማረች ኮንስትራክሽን እና ማኑፋክቸሪንግ የተመሠረተው በ 1996 ዓ.ም በ አቶ ብሩክ ዘውዴ እና ዐሥራ አራት መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ ከተግባረ ዕድ የቴክኒክ እና ሙያ ት/ቤት ጋር በመተባበር ብዙ የፈጠራ ሥራዎችን ሠርቷል እየሠራም ይገኛል። እንዲሁም ትልልቅ የማኑፋክቸሪንግ ማሽኖችን በመሥራት ለገበያ ያቀርባል። ቆየት ላሉ ማሽኖች ደግሞ የጥገና አገልግሎት ይሰጣል።
ተጨማሪለማ ጠቅላላ ባህላዊ ዕደ-ጥበብ
ድርጅቱ በጥቃቅን እና አነስተኛ ማኅበር በግለሰብ ደረጃ ተደራጅቶ ሥራ የጀመረው በ2009 ዓ.ም በአቶ ለማ መሥራችነት ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የባሕላዊ እቃዎችን በጥራት በማምረት ለገበያ ያቀርባል። ምርቱንም ሽሮሜዳ፣ ፖስታ ቤት እና መርካቶ አካባቢ በአዲስ አበባ እንዲሁም በክልል ከተሞች ደግሞ በባሕር ዳር፣ ሻሸመኔ እና ናዝሬት ለተረካቢዎች ያቀርባል። ድርጅቱ ከሌሎች የባህል ጌጣጌጥ አምራቾች የሚለየው …
ተጨማሪከድር ተማም የቤት እና የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ የቤት መገልገያ እቃዎች መሸጫ
ከድር ተማም የቤት እና የቢሮ መገልገያ እቃዎች የተመሠረተው በ 2005 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ ለቤት እና ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ኤክትሮኒክስ እና የኪችን እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀርባል።
ተጨማሪገነት ቆዳ እና የቆዳ ውጤቶች
ገነት ቆዳ እና የቆዳ ውጤቶች ድርጅት የተመሠረተው በ2007 ዓ.ም በወ/ሮ እመቤት ሽብሩ እና ሦስት አባላት ነው።ድርጅቱ በልደታ ክፍለ ከተማ ሥር የተመሠረተ ቢሆንም በጊዜው ብዙ ባዛር ልደታ ክ/ከተማ ባለመኖሩ ከልደታ ቦሌ ክ/ከተማ እየመጡ ነበር ባዛር የሚገለገሉት። ይህ ችግር ለማስወገድ ከቦሌ ክ/ከተማ ጋር በመነጋገር ወደ ቦሌ ክ/ከተማ ሊዘዋወሩ ችለዋል። ይህም ለድርጅቱ ሥራ …
ተጨማሪኤን ደብሊው አልሙኒየም እና ብረት ሥራ
ኤን ደብሊው አልሙኒየም እና ብረት ሥራ የተመሠረተው በ 2004 ዓ.ም. በሁለት መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ ሁለት ዓመታት በጥሩ ሁኔታ ምርት ሲያመርት መቆየቱን የድርጅቱ መሥራች አባል የሆኑት አቶ ነጋሽ ወንድምአገኝ አስረድተዋል። የአቶ ነጋሽ በሙያው ተገቢ የሥራ ልምድ መኖር፣ እንዲሁም ከድርጅቱ ምሥረታ በፊት የነበራቸው የስድስት አመት የሥራ ልምድ እና የቀለም እውቀት ተደምሮ …
ተጨማሪብሩክ ኤፍሬም እና ጓደኞቻቸው ቀርከሃ፣ እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ
ድርጅቱ የተመሠረተው በ 2013 ዓ.ም በአቶ ብሩክ ወልደ ሐዋርያት እና አራት መሥራች አባላት በአንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ካፒታል ነው። የሚያመርታቸው ምርቶች የቀርከሃ እና አጠቃላይ የእንጨት ሥራዎችን ነው። ድርጅቱ በቀን ሰላሳ ወንበር የማምረት አቅም አለው።
ተጨማሪሂሳሊስ ጋርመንት
ሂሳሊስ ጋርመንት የተመሠረተው በ 2010 ዓ.ም በወ/ሮ መሠረት ዳዱ ነው። ድርጅቱ የሚያመርታቸው የአልባሳት ምርቶች ከአንድ ዓመት እስከ አስራ ሦስት ዓመት ክልል ውስጥ ለሚገኙ ሕጻናት ነው። የአልባሳቶቹም ዋጋ የማኅበረሰቡን አቅም ያገናዘበ ነው። የአልባሳቶቹ ዋጋዎች ቢለያዩም ከዝቅተኛው ዋጋ መቶ ሰማንያ ብር (ብር 180) ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ዋጋ አራት መቶ ብር (ብር 400) …
ተጨማሪቴዎድሮስ፣ ኤልያስ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት
ቴዎድሮስ፣ ኤልያስ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ የተመሠረተው በ2008 ዓ.ም መጨረሻ ሲሆን፤ በጥሩ ሁኔታ ምርት የማምረት ሂደት የጀመረው በ2009 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ቴዎድሮስ ይሉ እና በአራት መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ ሲመሰረት ጠንካራ እንዲሆን ያደረገው ሁሉም የድርጅቱ መሥራች አባላት በአንድ የእድሜ ክልል እና የኢንጂነሪንግ ትምህርት ምሩቅ መሆናቸው …
ተጨማሪ