መነሻ / Yohannes Teshome (page 6)

Yohannes Teshome

ሰኢድ ሃሰን ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ሰኢድ ሃሰን በ2012 ዓ.ም. የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ሥራዎችን የሚሠራ ድርጅት ሲሆን በይበልጥ ደግሞ በፊኒሺንግ ሥራዎችን ላይ በሰፊው ይሳተፋል።

ተጨማሪ

ዐይናለም የዕደ ጥበብ ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በወ/ሮ አይናለም ሀብትህ ይመር እና ሦስት ጓደኞቻቸው በ2007 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች በሦስት ዘርፎች ሲሆኑ እነሱም ዕደ ጥበብ፣ የፈርኒቸር ሥራ እና የብረት ሥራዎች ናቸው።

ተጨማሪ

የአብሮነት ተምሳሌት በተግባር – ዮቶር የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ተቋም

ዮቶር በዋናነት በአነስተኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ የኅብረት ሥራ ማኅበሩ አባላት ንግዳቸውን የሚያንቀሳቅሱበት እና የሚያስፋፉበት እንዲሁም አብሮነታቸውን የሚያጠነክሩበት፤ ብሎም መካከለኛ የገንዘብ ዓቅም በማዳበር የትምህርት፣ የጤና እና ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለማሟላት የሚውል የገንዘብ አቅርቦትን ለመፍጠር በሠለጠነ የሰው ኃይል እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ጠንካራ የኀብረት ሥራ ማኅበር በመፍጠር እስከ 2026 ዓ.ም ድረስ የአባላቱን …

ተጨማሪ

ኑ በጋራ እንደግ – ጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር

goh-saving

ጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በኅዳር 6 ቀን፣ 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ማኅበራት ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 985/2009 ዓ.ም. አንቀጽ 10 መሠረት ጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በግ ታውቆ በመዝገብ ቁጥር አራ/1/1/750/2014 ዓ.ም ተመዝግቦ የተቋቋመ ነው።

ተጨማሪ

ጀንዲ ሌዘር

jendi-leather-logo

ድርጅቱ የተመሠረተው በወይዘሪት ናዲያ ይመር በ2012 ዓ.ም. ነው። ጀንዲ ሌዘር ጥራት ያላቸውን የቆዳ ውጤቶች በማምረት እና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ራሱን እና ማኅበረ ሰቡን እየጠቀመ ይገኛል። ወደ ፊት ደግሞ ለተጨማሪ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር እንዲሁም የሚያመርታቸውን ምርቶች ወደ ውጭ ሃገር በመላክ ለሃገሪቱ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት የበኩሉን አስተዋፅዖ የማበርከት እቅድ አለው።

ተጨማሪ

እሸት አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ.

እሸት አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. በ2000 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ አግኝቶ የቁጠባ እና ብድር አገልግሎት በመስጠት የገጠሩንና የከተማውን ማኅበረ ሰብ የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በመሥራት ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው።

ተጨማሪ

አብዲ፣ ከኪያ እና ጓደኞቻቸው የሌዘር ምርቶች

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ አብዲ ድሪባ 2012 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ነው። የሚያመርታቸው ምርቶች ጥራታቸውን የጠበቁ አጠቃላይ የቆዳ ምርቶች እንደ ጫማ፣ ጃኬት እና ቦርሳዎችን  ሲሆን፣ እንዲሁም ለቆዳ ሥራ የሚውል ጥሬ እቃ ያቀርባል።

ተጨማሪ