መነሻ / Tag Archives: ethiopia (page 11)

Tag Archives: ethiopia

ደቦ ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ.

debo-mfi

ደቦ ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አክስዮን ማኅበር የተቀላጠፈ የማይክሮፋይናንስ አገልግሎቶችን በመስጠት ለባለአክሲዮኖች ትርፍ ለማስገኘትና የደንበኞችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ለማሻሻል የተቋቋመ ተቋም ነው። ማኅበሩ በቀዳሚነት የተቀላጠፈና ውጤታማ የሆነ የቁጠባና የብድር አገልግሎቶችን ለደንበኞች ማቅረብ ዓላማው ያደረገ አክስዮን ማኅበር ነው። በአሁኑ ወቅት ደቦ ማይክሮፋይናንስ አዳዲስ አከባቢዎችና ማኅበረሰቦች ጋር በቀጣይነት ለመድረስና የተበዳሪዎችንና የተበዳሪ ቤተሰቦችን ኑሮ ሊያሻሽል …

ተጨማሪ

ዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማኅበር

ዳይናሚክ በአነስተኛና መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ገበሬዎች፣ በጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማትና ግለሰቦች ያለባቸውን የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ አለመሆን ችግር ለመቅረፍ ግልፅ እና ስትራተጂካዊ ራዕይ፣ ተልእኮና ዓላማ ቀርፆ ከግቡ የሚያደርሱትን የገንዘብ ቁጠባና ብድር አገልግሎቶች በመስጠት ላይ ይገኛል። የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ መሆን የተገለሉ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ለማብቃት፣ የመበልፀግ እድላቸውን ለማስፋትና …

ተጨማሪ

ምሳሌ የብድር አገልግሎት – ከዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናስ ተቋም አ.ማ.

ዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናስ ተቋም አ.ማ. የኅብረተ ሰቡን ፍላጎት ያማከለ የፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ተቋሙ የደንበኞቹን ፍላጎት መነሻ በማድረግ በየጊዜው አሠራሩን በቴክኖሎጂ እያዘመነ የሚገኝ ሲሆን አገልግሎቱን ለበርካታ የኅብረተ ሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ ቅርንጫፎችን እና የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት ላይ ይገኛል። ተቋሙ ወጣቱን የኅብረተ ሰብ ክፍል ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ በአሁኑ ሰዓት ምሳሌ …

ተጨማሪ

ቪዥን ፈንድ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማኅበር

vision-fund-logo

ቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአነስተኛ ገንዘብ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ 40/1988 የተቋቋመ አንጋፋ እና አስተማማኝ የገንዘብ ተቋም ነው። ተቋሙ በ91 አገልግሎት መስጫ የቅርንጫፍ ቢሮዎቹ አማካኝነት ተደራሽ እና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ተቋሙ በአሁኑ ሰዓት በጥቅሉ 734,226 በላይ የብድር እና የቁጠባ ደንበኞችን ለማፍራት የቻለ ሲሆን የሰጠው ብድር …

ተጨማሪ

መተማመን ብድርና ቁጠባ ተቋም አክሲዮን ማኅበር

metemamen-logo

መተማመን ብድርና ቁጠባ ተቋም ከብሔራዊ ባንክ ባገኘው ፈቃድ መሠረት ሁሉንም የኅብረተ ሰብ ክፍሎች በተለይም ሴቶችና ወጣቶች ለማገልገል የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ባሁኑ ወቅት በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ሕዝቦች እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጠቅላላው 29 ቅርንጫፎችና 4 ንዑስ ቅርንጫፎች ያሉት ተቋም ነው። ተቋሙ የኅብረተ ሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ህይወት ለመለወጥ አገልግሎት በመስጠት …

ተጨማሪ

ሞዛይክ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር

mosaic-construction

ሞዛይክ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተመሠረተው በአቶ ሳሙኤል ገዛህኝ እና በአቶ ጌትነት ካሳ መስከረም 2009 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ ደረጃ ስምንት ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ሲሆን የሚቀበላቸውን ሥራዎችን በጊዜ ገደባቸው እና በጥራት ሠርቶ ያስረክባል።

ተጨማሪ

አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ.

gears

አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማኅበር ዓላማ አድርጎ የተነሳው በልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሳተፍ ፍላጎት፣ ዕውቀት እና ሙያ ኖሯቸው በካፒታል እጥረት ምክንያት መሥራት ላልቻሉ ኢንተርፕራይዞች የተወሰነ የጊዜ ገደብና ቅድመ ሁኔታዎች አስቀምጦ የካፒታል ዕቃን በማቅረብ (በሟሟላት) የፋይናንስ እጥረታቸውን መቅረፍ ነው።  በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀው የሊዝ የፋይናንስ ስርዓት የካፒታል ዕቃዎች …

ተጨማሪ

ቢ ኤም ደብሊው (B.M.W) ሜታል ኢንጂነሪንግ

ቢ ኤም ደብሊው ድርጅት የተመሠረተው ጥር 2009 ዓ.ም. በአቶ አምሃ ወንድሙ እና በሁለት መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ የተለያዩ ማሽኖችን የማምረት እና የመጠገን እንዲሁም ለማሽኖች የመለዋወጫ እቃዎችን በራሱ ፈጠራ ይሠራል። እኒዚህም እቃዎች በአገር ውስጥ የማይገኙ እቃዎች ሲሆኑ ለእነዚህ እቃዎች የመለዋወጫ እቃ እና የተለያዩ ሞልዶች ያመርታል።

ተጨማሪ

“በከፍታ ፓኬጅ ተጠቅመናል”- መንግሥቱ እና ዳዊት ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ

መንግሥቱ እና ዳዊት ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የተመሠረተው በአቶ መንግሥቱ አባተ በ2009 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎች ጠቅላላ የኮንስትራክሽን ሥራዎች በዋናነት እንዲሁም የተለያዩ የአበባ ማስቀመጫ እቃዎችን በተለያየ መጠን እና ዲዛይን በተጨማሪም የህጻናት መጫወቻዎችን በጥራት ያመርታል።

ተጨማሪ