መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ (page 6)

የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ

የሲሚንቶ ዋጋ ተመን እና ቁጥጥር በአዲስ አበባ

cement-bag

መንግስት ካስቀመጠው የሲሚንቶ ዋጋ በላይ በሚሸጡ የሲሚንቶ አከፋፋዮች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ ፡፡ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በሲሚንቶ ግብይት ውስጥ ያሉ ህገ-ወጥ ደላሎችን ከገበያ ሰንሰለቱ በማስወጣት እየናረ የመጣውን የሲሚንቶ ዋጋ ለማስተካከል የመሸጫ ዋጋ በመተመን ከፋብሪካ አውጥተው የሚያከፋፍሉ የመንግስት የልማት ድርጅቶችና መመሪያውን አክብረው ለመስራት የተስማሙ የግል ነጋዴዎች …

ተጨማሪ

ለሲሚንቶ አቅርቦት እጥረት እና ዋጋ ጭማሪ መፍትኄ

cement-factory

በገበያ ላይ እያጋጠመ ያለውን የሲሚንቶ አቅርቦት እጥረትና ዋጋ ጭማሪ ለመፍታት የአቅርቦት መጠንን ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ። በኢፌዴሪ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አካላት የተመራ ልዑክ በገበያ ላይ የተከሰተውን የሲሚንቶ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ በአምራች ድርጅቶች ላይ የሥራ ጉብኝት አድርጓል፡፡ ለሁለት ቀናት የቆየው የሥራ ጉብኝት ዋና ዓላማም ለምርት እጥረቱ በምክንያትነት የሚነሱ ጉዳዮችን …

ተጨማሪ

“እንሥራ” የሸክላ ስራ ማእከል ተመረቀ

pottery

“እንሥራ” የሸክላ ስራ ማእከል ተመረቀ። የሸክላ ስራ ማእከሉ ግንባታው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀ ነው። የሸክላ ስራ ማእከሉን ኢ/ር ታከለ ኡማና ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች መርቀው ስራ አስጀምረውታል። በማእከሉ 1000 በሸክላ ስራ ላይ የተሰማሩ እናቶች የመስሪያና የመሸጫ ቦታዎች ከተሟላ የማምረቻ ቦታ ከተሟላ ቁሳቁሶች ጋር የሚያገኙ ይሆናል።

ተጨማሪ

ከስጋ እና ወተት ምርት 68.13 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኘ

meat_slaughterhouse

በ2012 በጀት ዓመት 11 ወራት ውስጥ ወደ ውጪ ከተላከ የስጋና ወተት ምርት 68.13 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒቴር ገለጸ፡፡ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የስጋና ወተት ኢንስቲትዩት የ2012 በጀት ዓመት የ11 ወራት የኤክስፖርት አፈፃፀምን በዘርፉ ከተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል፡፡ በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ከስጋና ወተት 113.81 ሚሊዮን …

ተጨማሪ

በኢትዮጵያ ዘላቂ የቡና እርሻ ሊቋቋም ነው

coffee-plant

ኤስ ኬ ፎረስት ኩባንያ የተባለው የደቡብ ኮሪያ የደን ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ ዘላቂ የቡና እርሻ ለማቋቋም ከኮሪያ የደን አገልግሎት ድርጅት ጋር በመቀናጀት እየሠራ ነው።፡፡ ኩባንያው እሮብ ዕለት እንዳስታወቀው በደቡብ ኢትዮጵያ የአካባቢው ተፈጥሮ እንዲያገግም ለማድረግ 700,000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ 70,000 የእጣን እና ሌሎች የዛፍ ችግኞችን ለመትከል አቅዷል፡፡ ለዚህም በቡና እርሻ ወስጥ …

ተጨማሪ

የኢትዮጵያን የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ማሳደግ የሚያስችል ዘመቻ ይፋ ተደረገ

textile_leather

የጨርቃ ጨርቅ፣ አልባሳትና ቆዳ ኢንዱስትሪ የሰራተኞች ማህበር ፌዴሬሽን የኢትዮጵያን የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ማሳደግ የሚያስችል ዘመቻ ይፋ አደረገ። ዘርፉን ከማሳደግ ጎን ለጎን አሁን ላይ የጤና ስጋት ከሆነው ኮቪድ19 ጋር ተያይዞ በሃገር ውስጥ ባሉ ፋብሪካዎች የጤና እና የደህንነት የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራን ማከናወንም የዘመቻው አላማ ነው ተብሏል። አሁን ላይ ኢትዮጵያ በኮቪድ19 ምክንያት የእንቅስቃሴ …

ተጨማሪ

ለኢንተርፕራይዞች ብቻ የወጣ ጨረታ

Arada Sub City

የአራዳ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በክፍለ ከተማው ሊያሠራቸው የሚፈልጋቸውን ልዩ ልዩ የግንባታ ሥራዎች እንዲሠሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ብቻ የሚያሳትፍ ጨረታ አውጥቷል።

ተጨማሪ

የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ የከተማ ግብርና መስፋፋት የሚቻሉባቸው መንገዶች ላይ ከባለሙያዎች ጋር መከሩ

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በይፋዊ ትዊተር ገጻቸው በትናንትናው ዕለት እንዳሰፈሩት፣ ከከተማ ግብርና ባለሙያዎች እንዲሁም በዘርፉ ተሰማርተው ውጤታማ ሥራዎችን ከሠሩ ግለሰቦች ጋር ተወያይተዋል። ምክትል ከንቲባው፣ “በየቅጥር ጊቢያችንና በጠባብ መኖሪያዎች ላይ ጭምር እንዴት የከተማ ግብርና መተግበር እንደሚቻል ተወያይተናል” ሲሉ አሳውቀዋል።

ተጨማሪ